ባለፉት ጥቂት ዓመታት በሁልም ዘርፍ እምርታዊ ለውጦችን አምጥተናል:- የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክበቡር አቶ ዘይኔ ቢልካ።
በግብርናው ዘርፍ በሌማት ትሩፋት፣በአዲስ ኢኒሼቲቭ ስራዎች፣በቅመማቅመም፣በቡናና ሌሎች ስራዎች ውጤታማ ማድረግ ተችሏል።
እንደሀገርም ሆነ እንደ ዞን የሴት አመራሮችን ከወንዶች እኩል ለማድረግ በተደረገው ጥረት ውጤታማ መሆን ችሏል።
በመሠረት ልማት ስራዎች በኢንቨስትመንት አዳዲስ ኢኒሼቲቭ ስራዎች ላይ አበረታች ለውጥ ታይቷል ያሉት አስተዳዳሪው በዞኑየስራ እድል ከመፍጠር ከንጻር አመርቂ ውጤት ታይቷል።
የዞኑን የሃይል አገልግሎት እንዲያገኝ በተደረገው ጥረት ሃያ አራት ሳትየመብራት አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ ተችሏል ብሏል።
አቶ ዘይኔ አክለውም የዲጂታል ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተሠራው ስራ ከ35ሺ በላይ ወጣቶችን አሳታፊ አድርጓል።
በመደመር መንግስት እንደ አጠቃላይ በሁሉም ዘርፍ የታዩ ውጤቶችን ከግብ ለማድረግ ብልጽግናን መምረጥ አለብን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል